የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

Jul 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመኸር እርሻ ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ተገኝ አባተ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በዞኑ በ2018/19 የምርት ዘመን ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በዚህምበመኸር እርሻ 231 ሺህ 566 ሄክታር መሬት በማልማት ከሰባትሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።

የዝናቡ ወቅት ቀድሞ በጀመረባቸው አካባቢዎችእስካሁን ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን ማሳ በዘር መሸፈኑንም ነው ያመለከቱት።

አርሶ አደሩ የተሻሻሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጅዎችን እንዲጠቀም በማድረግ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ከ160 ሺህ ኩንታል በላይ ዘመናዊ ማዳበሪያ መሰራጨቱን ነው የገለጹት።

የዝናብ መዘግየት ባለባቸው አካባቢዎችደግሞ የመስኖ አማራጭን በመጠቀም የመኸር ሰብል ልማቱን እንዲያከናውኑ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው የመኸር ምርት ዘመን ከለማው 231ሺህ ሄክታር መሬት አምስትነጥብ ስምንት ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026