የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኮሪደር ልማቱ ባሕርዳር ከተማን በቱሪዝም፣በንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል

Jul 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦የኮሪደር ልማቱ የባህርዳር ከተማን ውብና ጽዱ በማድረግ በቱሪዝም፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተመራጭና ተወዳዳሪ እንድትሆን ማድረጉን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሻገር አዳሙ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማቱ በጣና ሃይቅና አባይ ወንዝ የተከበበችውን ባህርዳር ከተማን ውበት ይበልጥ እንዲጎላ ያደረገ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ምእራፍ የኮሪደር ልማት ስምንት ነጥብ ስድስት ኪ.ሜ የሚሆን ስራ ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።

ደረጃቸውን የጠበቁ የሳይክልና የእግረኛ መንገዶች፣ የመንገድ ዳር ማረፊያዎች፣ መብራቶች ፣ፋውንቴኖችና ሌሎች የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎችን አካቶ መገንባቱ ከተማዋን ሳቢ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም የሶስተኛው ምእራፍ የኮሪደር ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ከተማዋን ይበልጥ ውብና ተመራጭነት ይበልጥ የሚያሳድግ እንደሆነም ነው የገለጹት።

ልማቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በከተማዋ ዘመናዊ የአኗኗር ስርዓት ግንባታን በማፋጠን እና የስራ ባህልን በመቀየር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስገንዝበዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኮሪደር ልማት ስራው ለ32 ሺህ ወጣቶች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር መቻሉንም ነው ያመለከቱት።

ህብረተሰቡም ይዞታውን በነጻ በመልቀቅ፣ በጉልበትና በሀሳብ ካደረገው ተሳትፎ በተጨማሪ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስገንዝበዋል።

የኮሪደር ልማቱ በፈረቃና በቅንጅት በመስራት የስራ ባህልን በመለወጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርከቷል ያሉት ደግሞ የኮሪደር ልማቱ ተቋራጪ ሳይት መሀንዲስ ዳሪክ ተስፋዬ ናቸው።


በኮሪደር ልማቱ በቫዞላ ንጣፍ ስራ የተሰማራው ወጣት ምሳው የኋላው በበኩሉ፤ የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ እድገትና ዘመናዊነት ላይ የራሴን አሻራ እንዳሳርፍ አድርጎኛል ነው ያለው።

ልማቱ በፈጠረላቸው የስራ እድልም ገቢያቸውን በማሳደግ ከራሳቸው አልፎ ሌሎችንም ተጠቃሚ ለማድረግ መቻላቸውን ገልጿል።


በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች በስፋት እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ የከተሞችን እድገት በማፋጠን በመሰረታዊነት ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026