የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የሱዳንን ግጭት ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤መስከረም 14/2017 (ኢዜአ)፦የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና የአሜሪካ መሪዎች የሱዳንን ግጭት ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰባቸውን ሱዳን ትሪቡን ከዋሽንግተን ዘግቧል።

የሁለቱ አገራት ፕሬዘዳንቶች በሱዳን ጉዳይ ላይ ትናንት ውይይት ማድረጋቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ፕሬዘዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ እና የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከውይይታቸው በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

መሪዎቹ በመግለጫቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ እደረሰ ባለው መፈናቀልረሀብና ጭካኔ የተሞላበት ግጭት ቆሞ ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ማለታችውን ዘግቧል።

"ለሱዳን ግጭት ምወታደራዊ መፍትሄ የለም" ያለው መግለጫው ጦርነቱ ባስቸኳይ እንዲቆም፣ ወደ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲመለስ እና በሲቪል የሚመራ አስተዳደር እንዲሸጋገር ጥሪ አቅርቧል።

በዳርፉር እየተባባሰየመጣው ብጥብጥም እንዳሳሰባቸው መሪዎቹ መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ሁለቱም ወገኖች ግጭት አቁመው ወደ ድርድር የማይመጡና የዓለም አቀፉን የሰብዓዊ ህግ የማያከብሩ ከሆነ የተለያዩ ማዕቀቦችን ከመጣል ጀምሮ በዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑም ጠይቀዋል።

ሰላማዊ ዜጎችን በተለይም ሴቶችን፣ ህጻናትን እና አረጋውያንን መጠበቅ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም አዘስገንዝበዋል።

በግጭት መስመሮች የእርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ሰብዓዊ ፋታዎች እንዲፈጠሩ የሁለቱ አገራት መሪዎች መጠየቃቸውን ሱዳን ትሪቡን በዘገባው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.