የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

<p>የባቡር መንገደኞች በፋይዳ መታወቂያ የትኬት አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓት ተግባራዊ ሊሆን ነው</p>

Feb 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።


የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) መንገደኞች በመታወቂያው አማካኝነት ኦንላይን ትኬት መቁረጥ እንደሚችሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።


ይህም የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱን ፈጣን፣ቀላል እና ይበልጥ ምቹ እንደሚያደርገው አመልክተዋል።


የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አገልግሎቱን በጋራ ማዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.