አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል።
በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱና ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች ተገኝተዋል።
በማሪታይም ባለስልጣን ስትራቴጂና ፖሊሲዎች ውስጥ ከተጠቅሱ የመፍትሄ ሃሳቦች ውስጥ በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ የድለላና የቅንጅት ጉድለቶችን መስመር በማስያዝ ተዋናዮችን የሚያገናኝ መተግበሪያ በማፍለቅ ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉ ተገልጿል።
በዚህም የትራንስፖርትና ሎጂስቲከስ ሚኒስቴር፣ የባለስልጣኑ፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም በመንግስት-የግል አጋርነት የሚፈጸሙ 40 የሚደርሱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፕሮጀክቶችን ጥቅም ላይ ማዋሉ ተገልጿል።
ፕሮጀክቶቹ በዘርፉ የመሰረተ ልማት ግንባታን፣ የአገልግሎት ማቀላጠፈያ ሥርዓትን፣ የጭነት እና የህዝብ ትራንስፖርት የአገልግሎት አቅም ግንባታ መርሃ ግብሮች የሚሳለጡበት እንደሆኑ ተነስቷል።
በዚህም መተግበሪያው በመንግስት ክትትል የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ያለውን የመረጃ ግንኙነት እና አገልግሎት የማሳልጥ የቴክኖሎጂ የአሰራር ሥርዓት መሆኑ ተመላክቷል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025