
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2017(ኢዜአ)፦ የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063 ዓላማን ለማሳካት የሚያስችል ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ገለጹ።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በሩሲያ-ሶቺ ከተማ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ተሳትፏል፡፡
ጉባዔው በሩሲያ እና አፍሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ያጎላ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በመድረኩ ገልጸዋል።

የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063 ዓላማን ለማሳካት የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኗን በመድረኩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአፍሪካ እና ሩሲያ መካከል በተለይም በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ዘርፎች ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የጋራ ተጠቃሚነትን ከፍ ለማድረግም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ትብብር ማሳደግ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ምርታማነትን ማሳደግ፣ እንደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ ኢንዱስትሪን ማስፋት የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን በመፍታት ረገድ ቁልፍ መስኮች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሻሻያ ለማድረግ እና አፍሪካ በድርጅቱ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና እንድታገኝ ሩሲያ ድጋፍ ለማድረግ ያላትን ዝግጁነት ኢትዮጵያ በደስታ ትቀበለዋለችም ነው ያሉት፡፡
ሚኒስትሩ ከጉባዔው ጎን ለጎን ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026