ሚዛን አማን፤ ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡- በሚዛን አማን ከተማ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ጠንካራ የሥራ ባህልን እያጎለበተ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ።
በከተማዋ በተለያዩ ምዕራፎች 34 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ አካል የሆነው የሦስት ኪሎ ሜትር ልማት ሥራ በ130 ሚሊዮን ብር የሚከናወን ይሆናል።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም እንደገለፁት፤ የከተማዋን መልካም ገጽታ ከፍ የሚያደርገው የኮሪደር ልማት ሥራ ጠንካራ የሥራ ባህልን እያጎለበተ ነው።
ከተማዋን ጽዱና ምቹ የመኖሪያ ቦታ ከማድረግ ባለፈ የቱሪዝምና የኮንፍረንስ ማዕከል ማድረግ የሚያስችል ተግባር በመከናወን ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሥራው በፍጥነትና በጥራት ተጠናቆ ለትውልድ እንዲሻገር የሚያስችል ቁጥጥር በባለሙያዎች እና አመራሮች እየተደረገ ነው ብለዋል።
በ34 ኪሎ ሜትሩ የኮሪደር ልማት ሥራ ነባር መንገዶችን የማስፋት፣ የእግረኛ መንገድ ግንባታና የአዲስ መንገድ ከፈታ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን የሚያካትት መሆኑን አክለዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራውም በኅብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወን መሆኑን ገልፀው የሀብት ማሰባሰብ ሥራው መጀመሩንም አቶ ግሩም ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው ለበርካቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የሥራ ትጋትን እየጨመረ ነው ያሉት ደግሞ የሚዛን አማን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቤሪ ናቸው።
ልማቱ በተጀመረ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረ ገልጸው፤ በየቀኑ ከ250 በላይ ሠራተኞች ይሰማራሉ ብለዋል።
በኮሪደር ልማቱ የስራ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል አቶ መንግሥቱ መስፍን፤ በማታ የግንባታ ሥራ ሠርተው ባያውቁም በዚህ የልማት ሥራ ግን መሥራት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ከማገኘው ገቢ ባሻገር የልማት ሥራውን በትጋትና በእኔነት ስሜት እየሰራሁ ለልጆቻችን ተሻጋሪ ልማትን ለማሳለፍ የኮሪደር ልማቱ ዕድልን ፈጥሮልኛል ሲሉ ተናግረዋል።
በልማቱ ምክንያት የስራ ዕድል ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ፤ ማታ ጭምር በመስራት የስራ ባህላቸውን ማሳደግ እንደቻሉም ገልፀዋል።
ሥራውን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ ለራሳችንና ለሕዝባችን የሚጠቅም መሆኑን አውቀን ሙሉ ጊዜያችንን በሥራ እያሳለፍን ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025