አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2017(ኢዜአ)፦ በከተማዋ የነዳጅ ምርት በመደበቅና በሌሎች ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ተሰማርተው ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የሚወሰደው ጥብቅ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለፀ።
የቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ የነዳጅ ስርጭትና ቁጥጥርን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በነዳጅ ስርጭት ላይ ልዩ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት በመዘርጋት በመዲናዋ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ጥረት መደረጉን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በአማካይ በቀን 3 ነጥብ 45 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ ለማደያዎች ሲቀርብ መቆየቱን ገልጸዋል።
ከዚህም ውስጥ በቀን በአማካይ 2 ሚሊየን ሊትር ናፍጣ እና 1 ነጥብ 45 ሚሊዮን ሊትር ቤንዚን መቅረቡን ጠቁመዋል።
በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተደረገው የቁጥጥርና ክትትል ሂደት በሕገ-ወጥ ተግባር ውስጥ የገቡ ነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
ለአብነትም በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 18 ሺህ 985 ሊትር ቤንዚን እና 9 ሺህ ሊትር ናፍጣ መወረሱን ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ከተገኘ 47 ሺ 608 ሊትር ነዳጅ ከ2 ሚሊየን 600 ሺ ብር በላይ በመሸጥ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል ብለዋል።
የነዳጅ ምርት በመደበቅ በከተማዋ ሰው ሰራሽ እጥረት በሚፈጥሩ፣ በቴሌ ብር በማይሸጡና ሀያ አራት ሰዓት በማይሰሩ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025