
ባህር ዳር ጥር 9/2017 (ኢዜአ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የአማራ ክልል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በበኩሉ ህብረተሰቡ ለግድቡ ግንባታ በቦንድ ግዥና በድጋፍ መልክ ይበልጥ እንዲሳተፍ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል ።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለሶስት ጊዜ የወር ደመወዛቸው ቦንድ በመግዛት አሻራቸውን ካሳረፉ የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች መካከል አቶ ሞላ አሞኘ አንዱ ናቸው።
የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በደረሰበት ደረጃ በመደሰታቸው በቀጣይም ግድቡ ለፍፃሜ እስኪበቃ አቅማቸው በሚፈቅደው ልክ ቦንድ ለመግዛት ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
"ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ምልክት ነው "ያሉት ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ አቶ ሞላልኝ አበጀ ናቸው።
ሰርተው ከሚያገኙት ገቢ ቀደም ሲል ለሁለት ጊዜ ያህል የ3 ሺህ 500 ብር ቦንድ በመግዛት ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።
የክልሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባይነህ ጌጡ በበኩላቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ድጋፉን በበለጠ እንዲያጠናክር እየተደረገ ይገኛል።
"የክልሉ ህዝብ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በቦንድ ግዥና በልገሳ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል" ብለዋል።
በክልሉ ህብረተሰቡ የግድቡ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ በቦንድ ግዥ፣ በልገሳና በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ከ39 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አስተዋፅኦ ማድረጉን አስታውቀዋል ።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026