አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር በሀገሪቱ የረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የፖሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ገለፀ።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገበያው በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ምህዳር ውስጥ ታሪካዊ እንደሆነ ጠቁመው፤ ባለሃብቶች ሙዓለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ነው ጥሪ ያቀረቡት።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የማክሮ ፖሊሲ ክፍል አስተባባሪ ተወልደ ግርማ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር በየደረጃው ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
ገበያው ማሕበረሰቡ ባለው ሃብት ልክ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፍና አቅሙን እንዲጠቀም ከማድረግ አንፃር ሰፊ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ነው የተናገሩት።
ከገንዘብ በተጨማሪም የንግድ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች በገበያው ውስጥ በመሳተፍ ሃብት ሊያፈሩ የሚችሉበት እድል እንደሚኖር በመጠቆም።
የካፒታል ገበያው ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አንፃር ዘግይቶ ቢጀመርም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች ጠንካራ በመሆናቸው የተሻሉ ስራዎችን መስራት የሚያስችል ሰፊ እድል መኖሩን ነው የጠቀሱት።
በተለይም የሌሎችን ልምድ በመቀመር ዘርፉን በፍጥነት ማሳደግ የሚያስችል በርካታ መንገዶች እንዳሉም ነው የሚናገሩት።
መንግስት በአሁኑ ወቅት በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ተግባራዊ እያደረገ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጠናክሮ በመቀጠል የካፒታል ገበያውን ማስፋፋት እንደሚችል ነው የጠቀሱት።
የካፒታል ገበያው በተለይ ለግል ባለሃብቱ የረዥም ጊዜ ብድር ከማስገኝት ባለፈ ኢትዮጵያ ላለመችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ስኬታማነት ጉልህ ሚና እንደሚያበረክትም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025