የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

<p>ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ተጀምሮ በኢትዮጵያውያን የሚጠናቀቅ የኩራታችን ምንጭ ነው - አቶ ገብረመስቀል ጫላ</p>

Jan 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ተጀምሮ በኢትዮጵያውያን የሚጠናቀቅ የኩራት ምንጭ ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ።

የክልሉ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ122 ሺህ ብር በላይ የቦንድ ግዢ ፈጽመዋል።

የቦንድ ግዢው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን በቀለ በተገኙበት ተከናውኗል።

አቶ ገብረመስቀል ጫላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ተጀምሮ በኢትዮጵያውያን የሚጠናቀቅ የኩራታችን ምንጭ ነው።


የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ለግድቡ ግንባታ ቦንድ በመግዛት አሻራቸውን በማስቀመጣቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.