መቀሌ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፡- ለ2017/18 የምርት ዘመን የተገዛ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ መሆኑን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ከደነው ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ለቀጣይ የምርት ዘመን ለክልሉ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ያስፈልጋል።
የፌዴራል መንግስት በግብርና ሚኒስቴር በኩል ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ የምርት ዘመን የግብርና ግብዓት እጥረት ያጋጥማል የሚል ስጋት እንደሌለ ጠቁመዋል።
በፌዴራል መንግስት ለቀጣይ የምርት ዘመን የሚሆን የተገዛ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ብሎም መጋዘን ወደ ተዘጋጀላቸው ወረዳዎች መጓጓዝ መጀመሩን ተናግረዋል።
ግብዓቱ ወደ ክልሉ በወቅቱ መግባት መጀመሩ ምርትና ምርታማነት መጨመር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
የክልሉ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን እና የፌዴራል መንግስትም የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ እያቀረበ መሆኑን አመልክተዋል።
የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ከሞዴል አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበራትና የምርምር ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
በክልሉ 2016/17 የምርት ዘመን የእርሻ ግብዓቶች በተለይ የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እንዲከፋፈል መደረጉ ለተገኘው የ13 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ከፍተኛ ሚና እንደነበረውም አቶ አበራ አውስተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025