አሶሳ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን ዘርፍ ላይ የተከናወነው የአሰራር ማሻሻያ ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አድማሱ ሞርካ ከለውጡ ወዲህ በዘርፉ ላይ የታየውን መሻሻል በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከለውጡ በፊት የክልሉ ህብረተሰብ በማዕድን ሀብት ተጠቃሚ አልነበረም፤ በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶችን ህብረተሰቡ አያውቅም ነበር ብለዋል።
የለውጡ መንግስት ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነውን የማዕድን ሀብት በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የአሰራር ማሻሻያ ማድረጉን ተናግረዋል።
በዚህም በክልሉ 400 የሚሆኑ ሰዎች ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሰው፤ ሚድሮክን ጨምሮ ትልልቅ ኩባንያዎች በክልሉ በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ መሰማራታቸውንም አክለዋል።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራትም 1ሺህ 697 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን አንስተዋል።
በተለይ ህገ-ወጥ ወርቅ አዘዋዋሪዎች ወደ ህጋዊ መንገድ በመግባት ወርቅን ወደ ብሄራዊ ባንክ ማስገባት መጀመራቸው ትልቅ ስኬት መሆኑንም አቶ አድማሱ ገልጸዋል።
ሌላው በክልሉ በስፋት የሚገኘውን የእምነበረድ ምርት ወደ ልማት ለማስገባት በአሶሳ ከተማ ፋብሪካ መቋቋሙን ተናግረዋል።
በድንጋይ ከሰል ምርት ከ500 በላይ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ወደ ስራ መግባታቸውን አንስተው ቢሮው አሁንም በክልሉ የማዕድን ሀብቶች በስፋት የሚገኙበትን ቦታ ለመለየት በጥናት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።
የማዕድን ሀብት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ያሉት ኃላፊው፤ የክልሉ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ክትትል እና ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከማዕድን ፍቃድ፣ የቦታ ቅኝትና ከአስተዳደራዊ ክፍያ 23 ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025