አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017 (ኢዜአ)፦የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሕንጻዎችን በፍጥነትና በጥራት ለመገንባት የሚያስችል የግንባታ ቴክኖሎጂ ባለቤት የሚያደርገውን ስምምነት ከጣልያኑ ዋንኮ ኢታሊ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ ቤት አሰራር ስልትን የሚያዘምን ግዙፍ የተገጣጣሚ ቤቶች ፋብሪካ ተከላን ለማከናወን ያስችለዋል።
የግንባታ ቴክኖሎጂው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማዘመን እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያግዝ ተመላክቷል።
ቴክኖሎጂው በቀን አንድ የሕንጻ ወለል መገንባት የሚያስችል ሲሆን ቪላ ቤትን ጨምሮ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች በአጭር ጊዜ መገንባት የሚያስችል መሆኑን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
ኮርፖሬሽኑ ከአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂ ቀጥሎ ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ያስተዋወቀው ሁለተኛው ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ እንደሆነም አስታውቋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ ጊዜን ፣ፍጥነትን እና ውጤታማ የበጀት አጠቃቀም መርህን በቀላሉ ለመተግበር የሚያስችሉ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።
የጣሊያኑ ዋንኮ ኩባንያ የሚታወቅበትን የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ተገቢውን ሳይንሳዊ ጥናትና ለዚሁ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችንም ኮርፖሬሽኑ ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል።
አስተማማኝ ግብዓት አቅርቦት ለመፍጠር ግዙፍ የግብዓት ማምረቻ ፋብሪካ በመትከል በቅርቡ ማስመረቁን አስታውሰዋል።
መሰል የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በማላማድ የወቅቱ የአገራችን የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት ኮርፖሬሽኑ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ረሻድ የገለጹት።
የፋብሪካ ተከላውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ወደ ሥራ ለማስገባት አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል።
የዋንኮ ኢታሊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማሲሞ ቡስነሌ በበኩላቸው የግንባታ ቴክኖሎጂውን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መንግስታዊውን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን መምረጣቸውን ገልጸዋል።
የፋብሪካ ተከላውን በአጭር ጊዜ ለማከናወን መዘጋጀታቸውን ገልጸው ፣ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኩል እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ተዘዋውረው እንደተመለከቱም ጠቁመዋል።
ፋብሪካው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን አካባቢ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ 10 ሄክታር ይዞታ ላይ እንደሚገነባ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025