ጥር 26/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ጎን ለጎን ግንዛቤ ለሚያሳድጉ ተግባራት ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ገልጿል።
የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የክልሉ የኢትዮ ኮደርስ ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጅማ ቱሉ በጉዳዩ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ኢንጂነር ጅማ ቱሉ በቆይታቸው የክልሉ ወጣቶች ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀት ጨብጠው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው ስልጠናውን መከታተል እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ተናግረዋል።
የአብይ ኮሚቴና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ከክልል እስከ ዞኖችና ከተሞች ስልጠናውን እያስተባበሩ መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህም በስልጠናው የመንግስት ሰራተኞች፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች፤ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መምህራንና ተማሪዎች እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናውን በኦንላይን መከታተል የሚያስችላቸው የመንግስት ተቋማት፤ ትምህርት ቤቶች፤ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና የወጣቶች ማዕከላት መዘጋጀታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።
እስካሁን በተሰራው ስራ 141 ሺህ የመንግስት ሰራተኖች፣ 84 ሺህ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ 30 ሺህ የቴክኒክና ሙያ መምህራንና ተማሪዎች የኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
እንደ ኢንጂነር ጅማ ገለጻ ዜጎች ስልጠናው በስፋት መውሰድ እንዲችሉ ሚኒ ሚዲያ፤ ማህበራዊ ሚዲያና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ግንዛቤ የማሳደግ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው።
በክልሉ ዞኖችና ከተሞች ህዝብ የሚበዛባቸውን አካባቢዎች በመለየት ለመርሃ ግብሩ አገልግሎት ብቻ የሚውል ኢንተርኔት መዘጋጀቱንም ጨምረው ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025