አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፦በመቀሌ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከ61 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የግንባታና የመስመር ዝርጋታ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሊሞን ተረፈ እንደገለጹት የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ከዚህ በፊት የነበረውን የውሃ አቅርቦት መጠንና ጥራት ይበልጡን የሚያሻሽል ነው።
በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ያለውን የውሃ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ለማሻሻል ከመቀሌ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ጋር በቅንጅት በመስራት ተጨማሪ የውሃ ጉድጓድ ለመጠቀም የሚያስችል የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች መጠናቀቃቸውን ስራ አስኪያጁ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ የውሃ ፕሮጀክቱን የመስመር ዝርጋታ የማጠናቀቅ ስራዎች መከናወናቸውንም ተናግረዋል።
ስራ አስኪያጁ አክለውም የውሃ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ተጨማሪ 20 ሊትር በሰከንድ ማመንጨት የሚችል መሆኑንና ይህም በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ያለውን የውሃ አቅርቦት ጥራትና ተደራሽነት እንደሚያሻሽለው መግለጻቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025