አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፡- ባዛርና ኤግዚቢሽኑ ማህበራት ምርቶቻቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገር እርስ በእርስ የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡
ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ዛሬ "የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አቶ ጃንጥራር አባይ በዚሁ ወቅት፤ በአዲስ አበባ ከተማ 2 ሚሊዮን አባላት ያሏቸው ከ 9 ሺህ በላይ ማህበራት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ማህበራት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች በማቅረብ ለዋጋ ንረት መረጋጋት አወንታዊ ሚና እየተጫቱ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል፡፡
በዛሬው እለት የተከፈተው ኤግዚቢሽንና ባዛር ማህበራት ምርቶቻቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገር እርስ በእርስ የገበያ ትስስር መፍጠር የሚያግዛቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
ዝግጅቱ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ህብረት ስራ ማህበራት የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ለሚደረገው ርብርብ ትልቅ አቅም ናቸው ብለዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት ህብረት ስራ ማህበራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ዛሬ የተጀመረው ኤግዚቢሽንና ባዛር አዲስ አበባ ከተማንና ክልሎችን በንግድ ለማስተሳሰር ትልቅ እድል እንዳለውም አመላክተዋል፡፡
ህብረት ስራ ማህበራት አምራቹንና ሸማቹን የሚያገናኙ ድልድዮች መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው፡፡
ማህበራቱ አምራቹንና ሸማቹን ከማገናኘት ባሻገር ለፋይናንስ ተደራሽነትና ለስራ እድል ፈጠራ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ዘርፉን ለማጠናከር የሪፎርም ስራ እንዲሰራ መደረጉንም ጨምረው አንስተዋል።
ኤግዚቢሽንና ባዛሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ11ኛ ጊዜ፤ በከተማ ደረጃ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025