ጥር 30/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታቀደውን ለማሳካት ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ ለኢዜአ እንዳሉት የክልሉ መንግስት እርሻውን ለማዘመንና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው።
ለዚህም ቢሮው አርሶ አደሩ የዝናብ ወቅትን ብቻ ከመጠበቅ ወጥቶ የውኃ አማራጮችን በመጠቀምበዓመት ሶስት ጊዜ ማምረት እንዲለምድና የሥራ ባህሉም እንዲለወጥ በየደረጃው ባሉ የዘርፉ አመራር አባላትና ባለሙያዎቹ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ የምርጥ ዘር፣ የተባይ ማጥፊያ፣ የአረም መከላከያና ሌሎች ግብዓቶችን የማሟላት ተግባራትን በጥናት ለይቶ በመተግበር ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ለአርሶ አደሩ ድጋፍ በማድረግና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተሻለ ውጤት መምጣቱን አብራርተዋል።
በዚህም በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አራት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ በእስካሁኑ እንቅስቃሴ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ምክትል ሃላፊው ገልጸዋል።
በልማቱ የአርሶ አደሩ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የአርሶ አደሩን የስራ ባህል ከመቀየርና ገቢያቸውን ከማሳደግ አንፃር ክፍተኛ ሚና ስላለው የመነቃቃት ስሜት ፈጥሮባቸዋል ብለዋል።
አርሶ አደሮቹ የበጋ መስኖ ስንዴውን መደበኛ ስራቸው አድርገው እንዲሰሩ በቅርበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህም በክልሉ በሁሉም ዞኖች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሮች ጭምር ልማቱ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025