
አዲስ አበባ፤የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለሚመጡ እንግዶች ቀልጣፋ የቴሌኮም እና የባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ኢትዮ- ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቁ።
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 8 እና 9/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለህብረቱ ጉባኤ ለሚመጡ እንግዶች ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር መሳይ ውብሽት፤ እንግዶች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከመድረሳቸው ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
በሚያርፉባቸው ሆቴሎችና በህብረቱ ዋና መስሪያ ቤትም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በማቋቋም የሲም ካርድና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በቀላሉ የሚያገኙበት ሥርዓት ከወዲሁ መዘርጋቱን ተናግረዋል።

የኢትዮ-ቴሌኮም የአገልግሎቶች ማረጋገጫ ቺፍ ኦፊሰር አበበ ያንባው፤ በህብረቱ ጉባኤ ለመታደም የሚመጡ እንግዶች በቆይታቸው ከኔትወርክ ጋር የተያያዘ የቴክኒክ ችግር እንዳያጋጥማቸው በቂ ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።
ለዚህም አስተማማኝ የ4 ጂ እና 5 ጂ ኔትወርክ በጥራት እንዲያገኙ በዋና ዋና ማዕከላት ማሻሻያ ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።
የአገልግሎት መቋረጥ እንዳይፈጠር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ የባለሙያ ስምሪት መሰጠቱን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል እንግዶች በቆይታቸው ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገልጿል።
በባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ዲቪዥን መርቻንትና ኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ብሌን ኃይለ ሚካኤል፤ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሬ እንዲፈጽሙ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሆቴሎችም የፖስ እና ሌሎች የዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን በመጠቀም ግብይትና ክፍያ የሚፈጽሙበት ዕድል መፈጠሩን ነው ያነሱት።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026