አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- ለረጅም ጊዜ የቆዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ፈተናዎችን ለመሻገር የለውጥ ሥራዎቻችንን በጠንካራ ትኩረት እና ባለቤትነት በመያዝ ቆራጥ፣ ሁሉን አቀፍ እና ታሪካዊ ርምጃዎችን ወስደናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ጉብኝት እንኳን ደህና መጡ ብለዋል።
አይኤምኤፍ ለኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራማችን የሚያደርገውን የቀጠለ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ የእርስዎንም የግል ጥረት እና አስተዋፅዖ ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጠዋለን ሲሉም ገልጸዋል።
በአይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ታላላቅ የድጋፍ መርሃ ግብሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም በሀገር በቀል ርዕይ እና የለውጥ አጀንዳ ላይ የተመሠረተ የእድገት እና የልማት ህልሞቻችንን በሚገባ ቀርፆ የያዘ ነው ብለዋል።
ለረጅም ጊዜ የቆዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ፈተናዎችን ለመሻገር የለውጥ ሥራዎቻችንን በጠንካራ ትኩረት እና ባለቤትነት በመያዝ ቆራጥ፣ ሁሉን አቀፍ እና ታሪካዊ ርምጃዎችን ወስደናል ሲሉም አክለዋል።
በፕሮግራሙ እስካሁን የታዩ ውጤቶችም ቀና እና አበረታች ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
እየተካሄዱ ያሉ የትግበራችን ሥራዎችም የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት፣ እድገትን ማፍጠን፣ የዜጎች ኑሮ ደረጃን ማሻሻል ሲሆኑ በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻል ናቸው ብለዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025