የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

<p>የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ</p>

Feb 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 02/2017(ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፖሊሲዎች፣ በኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና በግሉ ዘርፍ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድሎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ የስራ ጉብኝታቸውም አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እና የፖሊሲ ምክክሮችን በማድረግ የማይበገር እና ዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በትላንትናው ዕለት ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን እና ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026