አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና የጂኦስፓሻል ኢኒስቲትዩት የመሬትና መሬት ነክ መረጃዎችን የሚመዘግብና የሚያጋራ ዲጅታል የመረጃ ቋት(Portal) በይፋ ስራ አስጀመረ፡፡
ከኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ አንዱ ሀገራዊ የጂኦስፓሻል መረጃ መሰረተ ልማት በመዘርጋት አስቻይ የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ስርዓተ ምህዳር መፍጠር ነው።
በዚህም መሰረት የጂኦስፓሻል ዳታ መሰረተ ልማት በመዘርጋት ሀገራዊ የመሬት መረጃ አስተዳደርና ስርጭትን የሚያሳልጥ(ESRI Enterprise Portal) ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወደ ስራ አስገብቷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ ስትራቴጂ ቀርጻ እየሰራች መሆኗን አንስተዋል።
ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱ የልማት እቅድ ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያለው ማህበረሰብ ማፍራት ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ዕድገት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።
ዛሬ ይፋ የሆነው ዲጂታል የጂኦስፓሻል ፖርታል በኢትዮጵያ የመሬት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የማስተዳደር፣ የማጋራትና የመጠቀም አቅምን በእጅጉ የሚያሻሽል ነው ብለዋል።
የጂኦስፓሻል መረጃዎች ለውሳኔ ሰጪዎች ወሳኝ እንደሆኑ ጠቅሰው፥ በተለይም በከተማ ፕላን፣ በግብርና፣ በአደጋ ስጋት አመራር እና በአካባቢ ጥበቃ ስራ ላይ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ነው የገለጹት።
በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎትና የልማት ሥራን ለማፋጠን የመረጃ አያያዝ ስርዓት ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፥ በዚህ ረገድ ፖርታሉ ትልቅ እመርታን እንደሚያመጣ ጠቁመዋል።
መንግሥት የዲጂታል መረጃ አያያዝና ስርጭትን በአግባቡ መምራት የሚያስችሉ ፖሊሲና ህግጋትን በማዘጋጀት ወደ ተግባር ማስገባቱንም አንስተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላቸው ፀሐይ እንደገለጹት፤ ዲጂታል መሰረተ ልማቱ የጂኦስፓሻል ዳታ መሰረተ ልማት ዝርጋታን እውን በማድረግ ሀገራዊ የመረጃ አስተዳደርና ስርጭትን የሚያሳልጥ ነው።
ዲጂታል መሰረተ ልማቱ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን የተናበበ የመረጃ አጠቃቀም እንደሚያጎለብትም አመላክተዋል፡፡
በመሬት ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር መገኛውን ብቻ ሳይሆን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች ጋር አቀናጅቶ በመተንተን ትክክለኛ ውሳኔን ለማሳለፍ ያስችላል ነው ያሉት።
የጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት(ጂአይዜድ) የጂኦስፓሻል ፕሮጀክት አማካሪ ቱሉ በሻህ(ዶ/ር)፤ የመሰረተ ልማቱ ይፋ መሆን ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የመሬት አጠቃቀም እና ሌሎች ሀገራዊ የልማት እቅዶችን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025