የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

<p>በዞኖቹ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እና ክትትል ታግዞ በተሻለ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል</p>

Feb 11, 2025

IDOPRESS

ጊምቢ/ጅማ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ እና ጅማ ዞኖች የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እና ክትትል ታግዞ በተሻለ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የየዞኖቹ ግብርና ጽህፈት ቤቶች አስታወቁ።

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ145 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ዳግም መላኩ ለኢዜአ አንደተናገሩት በዘንድሮ የበጋ ወራት ከ182 ሺህ ሄክታር ባላይ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 145 ሺህ 790 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡


በዘር ከተሸፈነው መሬትም ከ6 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለማምረት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የታቀደውን ምርት ለማግኘትም የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በግብአት አቅርቦት በኩል ከ442 ኩንታል በላይ ምርጥ ዘርና 43 ሺህ 121 ኩንታል የአፈር መዳበሪያ እንዲሁም የተፈጥሮ መዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት በበጋ የተተገበረው የበጋ መስኖ ስንዴ ማልማት የአርሶ አደሩን ኑሮ እየለወጠ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡


የበጋ መስኖ ስንዴ ኢኒሼቲቭን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መሰራቱን የተናገሩት ደግሞ የጅማ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም ናቸው።

የመስኖ ስንዴው በአረምና በተባይ እንዳይጠቃ ከ34 ሺህ ሊትር በላይ የጸረ አረም መድሀኒቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ መደረጉን ተናግረዋል።

እስካሁን ከለማው መሬትም ከ11 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ አቶ ቲጃኒ አክለዋል።

በበጋ መስኖ ስንዴ የተሰማሩ የዞኑ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ሰብሉን ከአረምና ከጸረ ሰብል በሽታዎች ለመከላከል እየሰራን ነው ብለዋል።

በምዕራብ ወለጋ ዞን የበጊ ወረዳ አርሶ አደር ኑረዲን ከማል፤ ባለፉት አመታት ባለሙት የበጋ መስኖ ስንዴ ገቢያቸው በመጨመሩ በዘንድሮው አመት ግማሽ ሄክታር መሬታቸውን በስንዴ ማልማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የጊምቢ ወረዳ አርሶ አደር ገላና ሶቦቃ፤ በበኩላቸው ሶስት ሆነው በኩታ ገጠም ሁለት ሄክታር የሚጠጋ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.