
ባህርዳር ፤ጥር 3/2017 (ኢዜአ) ፡- በደብረብርሃን ከተማ ሲካሄድ በቆየው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በገቢ ማስገኛ ሥራዎች እራሳቸውን በመቻል ጥሪት እንዲያፈሩ ያገዛቸው መሆኑን በከተማው የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ተናገሩ።
በከተማው የመጀመሪያው ዙር የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ታቅፈው ጥሪት ያፈሩ 442 የቤተሰብ ሀላፊዎች ዛሬ ተመርቀዋል።
ፕሮግራሙ የምግብ ክፍተት በመሙላት የቤተሰብና የወል ጥሪት መገንባት ላይ ዓላማ አድርጎ የተነሳ ነው ፡፡
ትኩረቱም በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የምርት መቀነስ የሚታይባቸው አካባቢዎች የሚኖሩና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለጉዳት እንዳይጋለጡ መደገፍ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ይህን መሰረት አድርጎ በፕሮግራሙ የታቀፉ ወገኖች የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ አልፈው ሀብት በማፍራት ዛሬ በደብረብርሃን የተመረቁት ማሳያ ናቸው።
ተመራቂዎቹ በከተማ ግብርና፣በአገልግሎት፣ በንግድና በማንፋክቸሪንግ ዘርፎች በመሰማራት ከራሳቸው አልፎ ለአካባቢያቸው ወጣቶች የስራ እድል ፈጥረዋል።
ከፕሮግራሙ ተመራቂዎች መካከል አቶ አርጋው ገብሩ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ባገኙት ሥልጠናና የገንዘብ ድጋፍ የተሻሻሉ የወተት ላሞች በማርባት በቀን በአማካይ 17 ሊትር ወተት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከወተት ሽያጩ የሚያገኙት ገቢ ከእለት ፍጆታቸው አልፈው ከ500 ሺህ ብር በላይ መቆጠባቸውን አስረድተዋል።
ሌላኛዋ የፕሮግራሙ ተመራቂ ወይዘሮ ትግስት በቀለ በበኩላቸው፤ በከተማ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ታቅፈው ጠንክረው በመስራት ኑሯቸውን መለወጣቸውን ገልጸዋል።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በወቅቱ እንደገለጹት፤ በከተማ ሲካሄድ የቆየው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የስራ ባህልን በማሻሻል በማህበረሰቡ ዘንድ የቁጠባ ባህል እንዲጎለብት አግዟል።
ጥሪት አፍርተው ከፕሮግራሙ የተመርቁት ወገኖች በቀጣይ በሚሰማሩበት አዋጭ የስራ ዘርፍ በዘላቂነት ውጤታማ ሆነው እንዲቀጥሉ የአስተዳደሩ ድጋፍ እንደማይለያቸው ተናግረዋል።
የአስተዳደሩ ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ ዲባቤ፤ ተመራቂዎቹ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሰርተው ራሳቸውን በመቻል ጥሪት ያፈሩ 442 የቤተሰብ ሀላፊዎች መሆናቸውን አብራርተዋል።
አምቦ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ለንብ ማነብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ...
Jun 14, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርስ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የክልሉ ምክት...
Jun 11, 2026
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨ...
Jun 1, 2026
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ደግፎ የማብቃት ሥራው ተጠናክሮ እ...
May 26, 2026