ጎንደር፤ የካቲት 3/2017 (ኢዜአ)፡-የጎንደር ከተማን የመሬት ምዝገባ መረጃ ሥርአት በማዘመን የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ መሬት መምሪያ አስታወቀ፡፡
በከተማ መሬት ምዝገባና ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።
የመምሪያው ሃላፊ አቶ ትዛዙ በጽሃ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የከተማውን የመሬት ምዝገባ መረጃ ሥርአት ለማዘመን የዲጂታላይዜሽን ትግበራ እየተከናወነ ነው፡፡
በሁለት ክፍለ ከተሞች ከ5 ሺህ በላይ በሚሆኑ ይዞታዎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ወደ ኮምፒውተር የማስገባት ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው፣ በቀጣይም ወደ አራት ክፍለ ከተሞች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዘመናዊ የመሬት መረጃ ሥርአት የከተማ መሬትን በአግባቡ በማስተዳደርና በመምራት ህገ ወጥ የመሬት ወረራርንና ሀሰተኛ ሰነዶችን ከመቆጣጠርና ከመከላከል ባለፈ ለከተማዋ ልማት የላቀ አስተዋጾ አለው ብለዋል፡፡
"በተጨማሪም በመሬት ይገባኛል ሳቢያ የሚፈጠሩ የወሰን ግጭቶችን በመፍታት ለህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጥኖ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል" ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ በበኩላቸው፣ የዲጂታላይዜሽን ትግበራው ከተሞችን ለማልማትና የገቢ አቅምን ለማሳደግ አስተዋጾ እንዳለው ነው የተናገሩት።
የምዝገባ ስርአቱ እንዲሳካ አጋር አካላት ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበው፣ የከተማ አስተዳደሩ በበጀት፣ በሰው ሃይልና በቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተሞች አመራሮችን ጨምሮ ባለሙያዎችና አጋር አካላት መሳተፋቸው ታውቋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025