አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚመጥን በዲጂታል የታገዘ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስርዓት እየተገነባ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚያገናኝ የዲጂታል መተግበሪያ ሥርዓትን በይፋ ሥራ አስጀምሯል።
በዚሁ ጊዜ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር)፤ በዓለም ላይ እያደገ ለመጣው የህዝብ ቁጥርና የሰው ልጅ ፍላጎት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ቴክኖሎጂን መጠቀም የግድ ሆኗል ብለዋል።
ሀገራትም የተቋሞቻቸውን አገልግሎት ለማዘመን በየጊዜው አዳዲስ የዲጂታል ስርዓቶችን ወደ ስራ በማስገባት ላይ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያም bኋላ ቀር አሰራር የተነሳ የሚፈጠሩ የአገልግሎት መጓተት፣ የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ ከለውጡ ወዲህ ለቴክኖሎጂ ልማት ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።
ለአብነትም ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሀገሪቱን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚመጥን ቀልጣፋና ጠንካራ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስርዓት ለመገንባት የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ተገንብተዋል ነው ያሉት።
ዛሬ ይፋ የሆነው የጭነት ባለቤቶችንና የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችን የሚያገናኘው መተግበሪያም በዘርፉ ከተከናወኑ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ልማቶች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ፤ የዲጂታል ሥርዓቱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎትን እንደሚያሳልጥ ገልጸዋል።
የጭነት አገልግሎት ሰጪና ተገልጋዮችን በቀጥታ በማገናኘት የሶስተኛ ወገን ያልተገባ ጣልቃ ገብነትንና ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት ለማስቀረትም የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደጀኔ ሉጬ፤ ከዚህ ቀደም የጭነት ባለቤቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በቀጥታ የሚገናኙበት ዕድል ባለመኖሩ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ እንግልት ይፈጠር ነበር ብለዋል።
ዛሬ ወደ ስራ የገባው የዲጂታል ስርዓት የነበረውን እንግልት የሚቀርፍ፣ የደላላ ጣልቃ ገብነትንና አላስፈላጊ ወጪን በማስቀረት ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማኅበራት የቦርድ ፕሬዚዳንት ኤልሳቤጥ ጌታሁን፤ አዲሱ የትራንስፖርት ዲጂታል መሰረተ ልማት ለዘርፉ መዘመንና ዕድገት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣንና በዩናይትድ አፍሪካ ሎጂስቲክስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ትብብር የለማው የቴክኖሎጂ ሥርዓት "Digital Freight Marketplace systems" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025