የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦በሸገር ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ከ42 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ እየለማ መሆኑን የከተማው መስኖ ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አበራ ጫላ እንደገለጹት በከተማ አስተዳደሩ ለከተማ ግብርናም ሆነ ለበጋ መስኖ ልማት የሚያገለግል ውሃ ማቅረብ የሚያስችል ጥናት ተደርጓል።
በጥናቱ መሰረትም የአቅም ልየታ በማድረግ የገጸ ምድርና ከርሰ ምድር ውሃ በማቅረብ የመስኖ ልማት ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በተለይም በከተማው በኩራ ጅዳ፣ ለገ ጣፎ፣ ለገ ዳዲ እና በሰበታ ክፍለ ከተሞች ለመስኖ ልማት የሚውሉ ውኃ መቅረቡን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ 170 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማቅረብ ከ42 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ እየለማ መሆኑን አስታውቀዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የበጋ መስኖ ልማት እንደማይታወቅ አስታውሰው፤ ከተማው እንደ አዲስ ከተመሰረተ ወዲህ አርሶ አደሮችን በማሰልጠን ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
በተለይም የውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ ምንጮችን በማጎልበት፣ ወንዞችን በመጥለፍና የዝናብ ውሃን በማቆር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል።
በዚህም የዝናብ ውሃን ብቻ በመጠበቅ በዓመት አንዴ ሲያምርት የነበረው የአካባቢው አርሶ አደር በአሁኑ ወቅት የመስኖ ውሃን በመጠቀም በዓመት ሶስት ጊዜ ማምረት መቻሉን ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ስንዴ፣ አትክልትና ፍራፍሬን በበጋ መስኖ በብዛት በማልማት መቻሉንም ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025