መቀሌ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የመቀሌ ቅርንጫፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዲጂታል አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ ለደንበኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራትም 2 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ገልጿል።
በኮሚሽኑ የመቀሌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ምህረተአብ ገብረመድህን፤በቴክኖሎጂ የተደገፉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ደንበኞች ከውጭ የሚያስገቧቸው እቃዎች አሰራሩንም ሆነ የቀረጥና መጋዘን አገልግሎትን ጨምሮ አጠቃላይ ክፍያውን በተመለከተ በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው የሚስተናገዱበት አሰራር መዘርጋቱን ገልጸዋል።
በዚህ አሰራር መሰረት የቅርንጫፉ ባለሙያዎች ለደንበኞች በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም አስረድተዋል።
የደንበኞች ንብረትም ከወደብ እስከ መዳረሻው በቴክኖሎጂ የታገዘ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት አሰራር ተገባራዊ ሆኗል ብለዋል።
በአገልግሎት አሰጣጡ የሚሰበሰበው ገንዘብ ከፍ ማለቱን አንስተው፤ በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከእቅድ በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 1 ነጥብ 77 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ቢሆንም 2 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025