ጅግጅጋ፤ የካቲት 8/2017(ኢዜአ)፦በአገሪቱ ባለፉት ዓመታት ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን ለመፍጠር የተከናወነው ስራ አመርቂ ውጤት ማምጣቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ገለጹ።
የፌዴራል የክልልና ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት አስፈፃሚዎች የጋራ ምክክር መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት ባለፉት ስድስት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚወስዱ ምቹ መደላድሎችን ፈጥረዋል።
በተለይ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን ለመፍጠር የህግ ማዕቀፎችና ሌሎች የሪፎርም ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል።
በዚህም 85 የሚደርሱ የህግ፣ የፖሊሲ የሪፎርም ማሻሻያዎችና ማዕቀፎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው ይህም ለባለሃብቱ መደላደልን ከመፍጠር ባለፈ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ አስችሏል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አዋጅን የማሻሻል ስራም ለባለሃብቱ የዘርፍ ማስፋት ስራን ማምጣትንና በተለይም ቀደም ሲል የውጭ ባለሃብቶች በተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ የነበረው የኢንቨስትመንት እንቅሰቃሴ እንዲሰፋ ማስቻሉን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ባለፉት ዓመታት ዝግ የነበሩ የጅምላ እና ችርቻሮ እንዲሁም የወጪና ገቢ ንግድ ስርዓት መንግስት በወሰደው ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን የመፍጠር ስራ የውጪ ባለሀብቶች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ማስቻሉን አስረድተዋል።
በሌሎች ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ ይህም መንግስት በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ ቁርጠኛ ስራ እያከናወነ መሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
መድረኩ ጠንካራ ስራዎችን ለማጎልበት፣ ውስንነቶችን በጋራ ለመቅረፍ እንዲሁም ሚናን ለይቶ ለመንቀሳቀስና ቅኝታዊ አሰራርን ለመዘርጋት ታቅዶ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በበኩላቸው መንግስት የአገሪቱ ልማት እንዲፋጠን በሰጠው ትኩረት አጥጋቢ ውጤት ማሰመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
መንግስት ከሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ የልማት ስራዎች ባለፈ የባለሃብቱ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ባለሃብቱ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን እንዲያጎለብት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል።
በክልሉም ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን ለመፍጠር የህግና የአሰራር ማሻሻያዎችን በማድረግ፣የተፋጠነ የመንግስት አገልግሎት በመስጠትና የብድር አገልግሎትን በማመቻቸት የግል ባለሃብቱ በአምራች እንዱትሪ ውስጥ እንዲሰማራ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨትመንትና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025