አርባምንጭ፤ የካቲት 8/2017 (ኢዜአ):- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ሰባት ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ።
አዋጆቹ የኢንቨስትመንት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፣ የከተሞች ፈርጅ ለውጥ ረቂቅ አዋጅና ዝቅተኛ ተከፋይ የሆኑ የመንግስት ሠራተኞች ደምወዝ ማሻሻያ በጀት፣ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ረቂቅ ማቋቋሚያ፣ የመስኖ ውሃ አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ፣ የበጎ ፈቃደኝነት ፖሊሲና የክልሉ ስንደቅ ዓላማና አርማ ረቂቅ አዋጆች ናቸው።
የምክር ቤቱ የፕላን፣ መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዕንቁ ዮሐንስ የኢንቨስትመንት አስተዳደር አዋጅ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ያለውን ሚና ይበልጥ ለማጎልበት ታስቦ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።
የክልሉ ዕምቅ የተፈጥሮ ፀጋን ለኢኮኖሚ ዕድገት በማመቻቸት ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማምጣት ብሎም ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
የከተሞች ፈርጅ ለውጥ ረቂቅ አዋጅ የከተሞች ሁለንተናዊ ልማት እንደሚበጅ ገልጽው፤ በአዋጁ መሰረት አርባምንጭ፣ ወላይታ ሶዶና ዲላ ከተሞች በሪጂኦ-ፖሊስ ፈርጅ እንዲመደቡ ተወስኗል።
የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ማሻሻያ በጀት ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን ከፌዴራል መንግስት የተመደበውን 4 ቢሊዮን 204 ሚሊዮን 419 ሺህ 219 ብር በጀት ምክር ቤቱ አጽድቋል።
በተመሳሳይ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ማቋቋሚያ፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር፣ የበጎ ፈቃደኝነት ፖሊሲ እና የክልሉ ስንደቅ ዓላማና አርማ ረቂቅ አዋጆችም ጸድቀዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025