አርባምንጭ፤ የካቲት 8/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት የትምህርትና የጤና ልማት ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ መንግስት በተከናወኑ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ እየመከረ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ባለፉት ስድስት ወራት የትምህርትና የጤና ልማት ሥራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።
የትምህርት ተደራሽነትን በማስፋት ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ በክልሉ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 1ሚሊየን 619 ሺህ ተማሪዎችን መቀበላቸውን ተናግረዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥም መጽሐፍት በማባዛት ለአንደኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የተማሪ መጽሐፍ ጥምርታን አንድ ለአንድ ማድረስ መቻሉንም አንስተዋል።
በሌላ በኩል በጤና ልማት 587 ሺህ 931 ሴቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል።
በግማሽ ዓመቱ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለማከም በተደረገው ጥረት በ491 ሺህ 943 ሰዎች ላይ የወባ ምልክት የታየባቸው በመሆኑ አስፈላጊው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል።
የክልሉ ምክር ቤት አፌ-ጉባኤ ፀሐይ ወራሳ በበኩላቸው ምክር ቤቱ በሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
የምክር ቤት አባላት ክልሉን ከሙስና በማጽዳት ፈጣን ሁለንተናዊ ልማት እንዲረጋገጥ አበክረው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025