አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2017(ኢዜአ)፦ በሃላፊነት ዘመናቸው በአፍሪካ የሕዝብ የኑሮ ሁኔታ በሚያሻሽሉ ጉዳዮች ላይ ቀዳሚ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እና የአንጎላ ፕሬዚዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ ገለጹ።
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ መካሄድ የጀመረ ሲሆን ሞሪታኒያ የሕብረቱን ሊቀ መንበርነት ለአንጎላ በይፋ አስረክባለች።
የ2024 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የነበሩት የሞሪታኒያ ፕሬዚዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ ለአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ በ2025 የአፍሪካ ሕብረትን በሊቀ መንበርነት እንዲመሩ አስረክበዋል።
የአንጎላ ፕሬዚዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ እንዳሉት በጉባኤው ለአፍሪካ የሚበጁ ጠቃሚ ውይይቶች ተደርገዋል።
በሊቀመንበርነት ዘመናቸው የበለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ ስራ አጥነት፣ ግጭትን እና ህገ-ወጥ ስደትን ለመቀነስ እንደሚሰሩ ለአብነት ጠቅሰው፤ ዕቅዳቸውን ለማሳካትም የአባል ሀገራት ድጋፍ እንደማይለያቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የአፍሪካ 2063 አጀንዳዎችን ከግብ ለማድረስ ለሚደረገው ርብርብ በትኩረት እንደሚሰሩም ገልጽው፤ የህዝብ ኑሮ ለሚያሻሽሉ ተግባራት ቅድሚያ እንደሚሰጡ አንስተዋል።
የሰላም እና የጸጥታ ችግር ያለባቸውን የአህጉሪቱ ሀገራት ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲመለሱ እንደሚሰራም አመላክተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025