አዲስ አበባ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መሰረት መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን(ዶ/ር) ገለፁ።
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት "ሰው ሰራሽ አስተውሎት አካባቢን መፍጠር" በሚል መሪ ሃሳብ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ለግብርና ምርምር ማዕከል መሪዎችና ተመራማሪዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩም የግብርና ሚኒስቴር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል ።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ግብርና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል ።
ዘርፉን በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ፣ በጥናትና ምርምር የማዘመንና የማሸጋገር ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል ።
የአየር ፀባይ ለውጥ፣የመሬት መሸርሸርና የተባይ መከሰት የዘርፉ ተግዳሮት መሆናቸውን አመላክተዋል።
ተግዳሮቶቹን በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማረጋገጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎችና ምርምሮች መሰረት መሆናቸውን አስረድተዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የግብርና መረጃን በመተንተን፣የሃብትና ጊዜ ብክነትን በመቀነሰ፣ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የሚያስችል ውሳኔዎች እንዲሰጡ በማስቻል ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎትና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተረጋገጠ የምርት መጠንን መገመት፣ የእንስሳት ጤናንና የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና መንከባከብ ፣የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤዎችን ለመቅረፍ እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር የተቀመጠውን የዲጂታል ኢትዮጵያ ንቅናቄን እውን ለማድረግ፣ ዲጂታል ግብርናን እውን ለማድረግ፣ ፈጠራን ለማበረታታት እና የአርሶ አደሩን አኗኗር ለማሻሻል የዲጂታል ግብርና ፍኖተ ካርታ ይፋ መሆኑንም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ በበኩላቸው፥ ዓለም በፍጥነት በቴክኖሎጂ ለውጥ ውስጥ መሆኗን ተናግረዋል።
ጥናትና ምርምሮችን ጨምሮ ሁሉም ተግባራት በቴክኖሎጂ መጀመራቸውን ተከትሎ ከዘመኑ ጋር መሄድ እና ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የግብርና ዘርፉን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር ይገባል ብለዋል ።
ኢንስቲትዩቱ በ23 የምርምር ማዕከላት አማካኝነት በሰብል፣ በዓሳ፣ በእንስሳት፣በቡና፣ በቅመማ ቅመም፣ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በጥናትና ምርምር የተገኙ ምርቶችን የማባዛትና ለተጠቃሚዎች በማድረስ ለምርትና ምርታማነት መጨመር በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል ።
ስልጠናው የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እና የምርምር መሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ተገንዝበው በዛው ልክ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚነት እንዲጨምር የሚያስችል ነው ብለዋል ።
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚቆይ እንደሆነም ተመላክቷል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025