አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ 23ኛው የፋይናንስ ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
የወቅቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢንሼቲቭ ሊቀመንበርና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ጉባኤውን ሲከፍቱ ኢኒሼቲቩ ከአምስት አመታት በፊት እንደተመሰረተ ገልጸዋል።
ኢኒሼቲቩ በቀጣናው ያሉትን ሀገራት በኢኮኖሚ ትብብር የሚያስተሳስሩ የልማት ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚረዳ የሚኒስትሮች ማዕቀፍ ነው ብለዋል።
ኢኒሼቲቩ በልማት አጋሮች እንደሚደገፍም አቶ አህመድ ሺዴ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በጉባኤው የልማት አጋሮች ቃል ከገቡት 15 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ግማሽ ያህሉ መገኘቱንና ኢንሼቲቩን ሲደግፉ ከነበሩ 3 የልማት አጋሮች ወደ አምስት ማደጋቸውም ተመልክቷል፡፡
የኢንሼቲቩ የፕሮጀክት አፈጻጸም በአመዛኙ መልካም ቢሆንም የአንድ አራተኛ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግን አጥጋቢ በሚባል ደረጃ ላይ ባለመሆኑ ይህንኑ ማሻሻልና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ በጉባዔው ላይ ተገልጿል፡፡
በስብሰባው የቀጣናውን የልማት ትስስር ለማሳደግና ኢኒሼቲቩን ለማጠናከር የአየር ንረት ለውጥ እቅዶችንና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሚጠቅሙ አዳዲሰ የፋይናንስ አማራጮች የበለጠ በሚሰፉበት፣ ተጨማሪ ቀጣናዊ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ስለሚደረጉበት እንዲሁም ከአጋሮች የተጠናከረ ድጋፍ በሚፈለግባቸው ዘርፎች ላይ አቅጣጫ መቀመጡም ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ ቀንድ ኢንሼቲቭ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን መናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025