
አዲስ አበባ፤የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ፋይዳ መታወቂያ ተአማኒነትን ለማጎልበትና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ገለፀ ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር " ፋይዳ ለኢትዮጵያ " በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ፥ ፋይዳ ዜጎች ወጥ ማንነት እንዲኖራቸውና በዛው ልክ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።
አገልግሎቱ ከተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር አሰራራቸውን ለማዘመንና ለማስተሳሰር በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የአገልግሎቱ የባለድርሻ አካላት ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ሳሚናስ ሰይፉ ከ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆናቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይም የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ገቢዎች ሚኒስቴር ከፋይዳ ጋር በቅንጅት ከሚሰሩ ተቋማት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ሻፊ፥ ተቋሙ ከህዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ አሰራሩን ከፋይዳ ጋር ማስተሳሰር በመቻሉ ከዚህ ቀደም ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮች ሙሉ በሙሉ መቀረፋቸውን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመርቻንት እና ኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ብሌን ሀይለሚካኤል፥ የደንበኞቻችንን ማንነት በትክክል በማወቅ አካውንት ለመክፈትና የብድር አገልግሎት ለመስጠት ፈይዳ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ከፋዮችና ምዝገባ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ፋና፥ ተቋማቸው ከአገልግሎቱ ጋር ትስስር በመፍጠር የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የታገዙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ ሺህ በላይ የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያዎች ተከፍተው ምዝገባ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026