አዲስ አበባ፣የካቲት 12/2017 (ኢዜአ)፦የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ራይነር የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ እና ልዑካቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ባደረጉት ጉብኝት፤ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል እና የተግባራዊ በረራ ማሰልጠኛ ምስለ በረራዎችን መመልከታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።
በወቅቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘመናዊ አውሮፕላኖቹ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ሂትሮው፣ ለንደን ጋትዊክ እና ማንቼስተር ከተሞች 16 ሳምንታዊ በረራ በማድረግ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025