አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፡- በመንግስት እና የግል አጋርነት ከሚለሙ ስምንት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እስከ 750 ሜጋ ዋት ኃይል ለማግኘት መታቀዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የተቋሙ የመንግሥት እና የግል አጋርነት መምሪያ የፀሐይና ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዘውዴ እንደገለጹት የኃይል ስብጥርን ለማሳደግ እና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት በኃይል ማመንጨት ዘርፍ የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል።
እየተተገበረ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ የውጭ ምንዛሬ አካውንት ለመክፈት አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቁመው ፕሮጀክቶቹን ወደ ትግበራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በዚህም በመንግስትና በግል አጋርነት የሚለሙ ስምንት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መለየታቸውን ጠቁመዋል።
የጋድ 1 እና 2፣ ዲቼቶ እና ወራንሶ(የአራት ፕሮጀክቶች) ጥናታቸው መጠናቀቁንም አቶ አሸናፊ ገልጸዋል።
የጋድ 2 እና ወራንሶ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመንግስት እና በግል አጋርነት ለማልማት ጨረታ መውጣቱንም ተናግረዋል።
ሁለቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች 225 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳላቸውና ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ 200 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
ፕሮጀክቶቹ በመንግስትና የግል አጋርነት መልማታቸው በተሻለ ጥራትና ጊዜ ለማጠናቀቅ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።
ከስምንቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች እስከ 750 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ዕቅድ መያዙን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025