አዲስ አበባ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፦በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ የስራ አመራር ልዑክ የኮምቦልቻ ከተማ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ትግበራን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መሀመድ አሚን የሱፍ ተገኝተዋል።
ኩባንያው እና የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሚያከናውኑት የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
ቀሪ ስራዎችም በአፋጣኝ ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ መቀመጡን ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ፕሮጀክቱ ኮምቦልቻን ለኢንዱስትሪና ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ይበልጥ ተመራጭ በማድረግ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ከተማ እንድትሆን ያደርጋታል ነው የተባለው።
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክቱ የመስተዳድሩን አገልግሎቶች፣የግብር አሰባሰብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ክፍያዎችን በቴሌብር በማቀላጠፍ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እንደሚቆጥብም እንዲሁ።
የአሰራር ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን በመጨመር ረገድ አስተዋጽኦ እንደሚያበርክት ተነግሯል።
ልዑኩ በከተማዋ የሚገኝ የአረንጓዴ ልማት ፓርክ መጎበኝቱን ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025