አዲስ አበባ፤የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የንግድ እና ኢንቨስትመንት የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።
የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ ፎረም በላሆር ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።
ፎረሙ በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በፓኪስታን የንግድ ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ ነው።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በፎረሙ ላይ ለተሳተፉ የፓኪስታን የንግድ ማህበረሰብ አባላት ኢትዮጵያ ያደረገቻቸው የኢኮኖሚ ሪፎርሞች በሀገሪቷ የፈጠረውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምቹነት አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።
በግብርና እና ግብርና ማቀነባበሪያ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን ቱሪዝም እና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሰፊ እድሎች እንዳሉ አመልክተዋል።
የአማራጭ ኃይል አቅርቦት፣ የህዝብ ቁጥር ብዛት፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል እና አፍሪካን እርስ በእርስ እና ከተቀረው ዓለም ጋር የሚያስተሳስረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለፓኪስታን ባለሀብቶች ኢንቨስትመት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና አባል ሀገር መሆኗ እና በአህጉሪቷ ግዙፉን አየር መንገድ መያዟ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ያደርጋታል ነው ያሉት አምባሳደሩ።
አምባሳደሩ የፓኪስታን ባለሀብቶች በአዲስ አበባ በሚዘጋጀው የኢትዮጵያን ምርቶች እና አገልግሎት የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ (Single Country Exhibition) ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አውደ ርዕዩ የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያስችል ገልጸዋል።
የፓኪስታን የንግድ ልማት ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል አብዱል ከሪም ሜሞን ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት መካከል እንደምትጠቀስ ገልጸዋል።
የፓኪስታን ባለሀብቶች የኢትዮጵያን የንግድ እና ኢንቨስትመንት እድሎች ለመመልከት ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል።
ባለሀብቶች የኢትዮጵያን ምርቶች እና አገልግሎት የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውን በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025