አዲስ አበባ ፤የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓቱን ለማሻሻል የተጀመረው ሥራ በፍጥነት ወደ ተግባር ሊገባ እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዘርፎች አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አፈፃፀም በመጀመሪያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሪፎርሙ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ወደ ተግባር ለመቀየር የተደረገው ጥረት አበረታች
ነው፡፡
በዘርፉ የሚሰጠው ስልጠና የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልስ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የስልጠናውን ጥራትና አግባብነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ ነው ያሉት ሚኒስትሯ የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓቱን ለማሻሻል የተጀመረው ሥራ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ግብዓትና ግብይት ላይ ያተኮረ የሙያ ደረጃና ስርዓተ ስልጠና ዝግጅት፣ ተቋማትን በአንፃራዊ የመልማት ፀጋ ለማደራጀት የተጀመረውን ሥራ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር፣ የማሰልጠኛ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ ሥራ የገበያ ክፍተቱን በሚሞላ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት በሚፈለገው ደረጃና ጥራት እንዲያከናውኑ ድጋፍና ክትትል ማድረግ የዘርፉ የቀጣይ ወራት ትኩረት እንደሆኑ መገለፁን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025