ዲላ፤ የካቲት 19/2017 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሉ የግብርና ልማት ተግዳሮቶችን በመፍታት ምርታማነትን ለማሳደግ መረባረብ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ።
"የግብርና ምርታማነት ለብልፅግናችን" በሚል መሪ ቃል የክልሉ የ2017 ዓ.ም የበልግ አዝመራ ተግባራት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት በክልሉ ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገ ጥረት ውጤት ተመዝግቧል።
ይሁንና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የተባይና የአረም ቁጥጥር፣ የቴክኖሎጂ አጠቀቀም ውስንነት እንዲሁም የድህረ ምርት አያያዝና የገበያ ትስስር በክልሉ የግብርና ልማት ፈተናዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
እነዚህን የግብርና ልማት ተግዳሮቶች በመፍታት የበልግ እርሻ ምርታማነትን ለማሳደግ ባለድርሻ አካላት በርብርብ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት ለመውጣት በሚደረገው ጥረት በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ የልማት አርበኛ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው ክልሉ በሀገር ደረጃ ያለውን የምርት ድርሻ ለማሳደግ ለበልግ አዝመራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።
በተለይ የሜካናይዝድ እና የኩታ ገጠም እርሻ ልማትን ከማጠናከር ባለፈ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሻሻል ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በዚህም በተያዘው የበልግ እርሻ በክልሉ ከ848 ሺህ 155 ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ከ77 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል።
ለዕቅዱ ስኬታማነት የምርምር ተቋማት፣ የግብርና ሴክተርና ባለድርሻ አካት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025