የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

<p>ኢትዮ ቴሌኮም የተቋማትን አገልግሎት የሚያቀላጥፉና ምርታማነትን የሚያጎለብቱ ዲጂታል አሠራሮችን አጠናክሮ ይቀጥላል</p>

Feb 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም የተቋማትን አገልግሎት የሚያቀላጥፉና ምርታማነትን የሚያጎለብቱ የዲጂታል አሠራሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለፁ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ይህን ያሉት ኩባንያው በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን አገልግሎት አሰጣጥ የሚያቀላጥፉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ዛሬ ይፋ ሲያደርግ ነው።


የኢትዮጵያን የእንስሳት ሃብት አስተዳደርን ማዘመን የሚያስችል ዲጂታል የእንስሳት መከታተያ አማራጭ ይዞ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እምቅ የእንሰሳት ሃብት ያላት ሀገር መሆኗን ጠቁመው፤ ቴክኖሎጂው ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ይበልጥ ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።


በዘርፉ ያለውን የፋይናንስና የኢንሹራንስ ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር እና አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቀላሉ እንዲገናኙ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማረጋገጥ ኢንተርፕራይዞችን ብቁና ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ወሳኝ መሆኑንም ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ያነሱት፡፡

ለዚህም ኢትዮ-ቴሌኮም የኔትወርክ ሽፋንና ተደራሽነቱን በመጠቀም የህክምና፣ የኮንስትራክሽንና ተያያዥ አገልግሎት ለሚሰጡ ኢንተርፕራይዞች በቦታ ያልተገደበ ፈጣን የድምፅና የምስል አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ቴክኖሎጂን ይበልጥ በማዘመን ይፋ ማድረጉን ተናግረዋል።

ባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ምንም አይነት የቴሌኮም መሰረተ ልማት ሳያስፈልጋቸው በኢትዮ-ቴሌኮም መሰረተ ልማት ብቻ ተጠቅመው አገልግሎታቸውን ማስፋት፣ ማስተዋወቅና ለህብረተሰቡ በፍጥነት ተደራሽ የሚያደርጉበትን መፍትሔ ማምጣቱንም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ትምህርት ቤቶች ከተማሪዎችና ከወላጆች እንዲሁም ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በቴክኖሎጂ በቀላሉ ማገናኘት የሚያስችል አገልግሎት መዘርጋቱንም ነው የጠቆሙት።

የኢንተርፕራይዞችን ተግባቦት የሚያቀላጥፍ፣ ስራን የሚያሳልጥና በጊዜና በቦታ ያልተገደበ የመረጃ ልውውጥ በቪዲዮ፣ በድምፅ፣ በጽሁፍ እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስርዓት ይፋ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣይም የተቋማትን አገልግሎት የሚያዘምኑ እና ዘላቂ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑ የዲጂታል አሠራሮችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


የኩባንያው የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ታምራት ተስፋዬ በበኩላቸው ኩባንያው አዳዲስ አገልግሎቶችን ሲጀምር የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት የዳሰሳ ጥናቶችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


በቀጣይም የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን የሚያረጋግጡ ዘመናዊ አሰራሮችን ይፋ ማድረጉን እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡


በሁነቱ የተገኙ የኢትዮ-ቴሌኮም የፕሪሚየም ደንበኞች ፋሲል ተኮላና ሚፍታህ ደንድር ይፋ የተደረጉት ቴክኖሎጂዎች ስራቸውን የበለጠ ለማቀላጠፍ እንደሚያግዟቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.