ጅማ፣የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦የጎንደር ከተማ የስራ ሀላፊች በጅማ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የልምድ ልውውጥ አደረጉ።
በጎንደር ከተማ ከንቲባ በአቶ ቻላቸው ዳኘው የተመራ የስራ ኃላፊዎች ቡድን የጅማ ከተማን የኮሪደርና ልማትና ሌሎች የከተማ ግብርና ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
ከንቲባው በወቅቱ እንዳሉት፥ በጅማ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣የከተማ የግብርና እንዲሁም የሴፍቲኔት እንቅስቃሴ ለሌሎች ከተሞችም ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ነው።
ሁለቱ ከተሞች በኢትዮጵያ ካሉ ጥንታዊ ታሪክ ያላቸው ከተሞች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰው፥ በጅማ ከተማ ያደረጉት ጉብኝትም የከተማ ልማት ስራ ልምድን ለመለዋወጥ እና ለእርስ በርስ ትስስር የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም በጅማ ከተማ የኮሪደር እና የአረንጓዴ ስፍራዎች ልማት ለሌሎች ከተሞችም መልካም ተሞክሮ መሆን የሚችል ነው ብለዋል።
የጅማ ህዝብ የልማቱ ባለቤት በመሆንና የአመራሩ ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።
በከተማዋ የንብ ማነብ ስራን ለማዘመን የዘመናዊ ቀፎ ተደራሽነት፣ የቆሻሻ ማስወገጃና መልሶ በመጠቀም ለተፈጥሮ ማዳበሪያነት ለማዋል የሚያስችል ፕሮጀክት እና የኮሪደር ልማቱ ልዩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ሲሉም አክለዋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሀ ቀመር በበኩላቸው፥ ጉብኝቱ አብሮነትን ለማጎልበትና በተሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ልምድን የምንለዋወጥበት ነው ብለዋል።
በጅማ ከተማ የኮሪደር፣የሴፍቲኔት ፕሮግራም፣ የከተማ ግብርናና ሌሎች የልማት ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
ጉብኝቱ የሁለቱን ከተሞች ትስስር በይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር መልካም የልማት ስራ ልምድ ልውውጥ የሚደረግበት እንደሆነም አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025