አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተዘረጉ መሰረተ ልማቶች እና የተነደፉ ስትራቴጂዎች የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚያሳኩ መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
በሀገር ውስጥ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመዘርጋት እና ድንበር ተሻጋሪ የኢ-ኮሜርስ ንግድን ማሳለጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዲጂታል አፍሪካን ዕውን ማድረግ ፖሊሲ አውጭዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና መሪዎች ተገናኝተው በጋራ የሚመክሩበት ዓለም አቀፍ መድረክም ታዘጋጃለች ብለዋል፡፡
ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ የሚያግዙ የኢ-ኮሜርስና የኤሌክትሮኒክ ስትራቴጂዎች ጸድቀው ሥራ ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
ስታርት አፕ፣ የአምስት ሚሊዬን ኮደርስ ስልጠና የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያቀላጥፉ አስቻይ ሁኔታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተዘረጉ መሰረተ ልማቶች እና የተነደፉ ስትራቴጂዎች የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚያሳኩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ በመንደፍ እና ተቋም በመገንባት ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ተቋም በመገንባት፣ በግሉ ዘርፍ መካከል ጤናማ ውድድር ማድረግ የሚያስችል ሥነ ምህዳር በመፍጠር ከራሷም አልፎ ለአፍሪካውያን ልምድ የሚሆን አቅም ገንብታለች ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025