ሶዶ፤ የካቲት 24/2017 (ኢዜአ):-በወላይታ ዞን ከ1 ሺህ 200 ሄክታር በሚበልጥ መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በዞኑ እየተከናወነ ያለውን የመስኖ ልማትና ሌሎች ተያያዥ የግብርና ሥራዎች በተመለከተ የዞኑ የግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ ታምሩ መለቆ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በማብራሪያቸውም በዞኑ የመስኖ ልማትን ለማጠናከር አርሶ አደሮችን በማደራጀት አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዞኑ ለበጋ መስኖ ስንዴ የምርጥ ዘር እና ሌሎች ግብአቶች ቀደም ብለው ተደራሽ መደረጋቸውን አስታውሰው በዚህም 1 ሺህ 233 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ሰብል መሸፈኑንና 61 ሺህ ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የዱጉና ፋንጎ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ `ኃላፊ አሸናፊ ብዙነህ እንደገለጹት፤ በወረዳው 1ሺህ 252 ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እያከናወኑ ይገኛሉ።
በወረዳው ደንዶ ኮይሻ ሁምቦ እና ጨርቻ ቀበሌዎች በማህበር የተደራጁ ወጣቶች በብላቴ ወንዝ ዳር የበጋ መስኖ ስንዴ እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በማህበር የተደራጁት 12 ወጣቶች በ40 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በመስኖ እያለሙ መሆናቸውንና ከልማቱም ጥሩ ውጤት እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የማህበሩ ሰብሳቢ አስራት ዘውገ ለልማቱ ቀደም ብሎ የአፈር ማዳበሪያና ዘር መቅረቡን አስታውሶ ከዘንድሮው የመስኖ ልማት ከ1 ሺህ 380 ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንጠብቃለን ብሏል።
የማህበሩ አባል መንግስቱ ሻካ በበኩላቸው በየደረጃው በአመራሩና በባለሙያዎች በተደረገላቸው ድጋፍ በብላቴ ወንዝ ዳርቻ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
"በልማቱም ጠንክረን በመስራታችን ጥሩ ውጤት እንጠብቃለን ሲሉ" ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025