መቱ፤ የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ቡና አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ቡናን በጥራትና በብዛት ለማምረት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።
በብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊን ጨምሮ የክልልና የዞን የስራ አመራር አባላት የመቱ-ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታንና በመቱ ወረዳ እየተከናወነ የሚገኘውን የቡና ተክል ዕድሳት ስራን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ኃላፊው አቶ ነመራ ቡሊ እንዳሉት ከተያዙት የግብርና አቅጣጫዎች ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው የልማት ተግባራት መካከል ቡና አንዱ ነው።
በክልሉ ቡና አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ቡናን በጥራትና በብዛት ለማምረት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም አርሶ አደሮችና በቡና ልማት ላይ የተሰማሩ አካላት የቡና ጥራትን ለማስጠበቅ ትልቅ ተኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አስረድተዋል።
በተያያዘ ዜና የስራ ኃላፊዎቹ የመቱ-ጎሬ አየር ማረፊያ የግንባታ ሂደትን የተመለከቱ ሲሆን ግንባታው እየተፋጠነ መሆኑም ተመልክተዋል።
የመቱ-ጎሬ አየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አስመላሽ አባይ፤ ግንባታው ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ 69 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።
በአንድ ዓመት ውስጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የኢሉአባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ የመቱ-ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሌላ ተጨማሪ የልማት ዕድሎችን ይዞ የሚመጣ መሆኑን አንስተው በቱሪዝም፣ በኢንቨስትመንትና በግብርና ጭምር መነቃቃትን የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል።
በኢሉአባቦር ዞን በተያዘው ዓመት በ16 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የቡና ዕድሳት ስራ በጉንደላ እና በንቅለ ተከላ የሚከናወን መሆኑን የገለጹት የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጫሊ ናቸው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025