ቡታጅራ፤ የካቲት 26/2017 (ኢዜአ)--በቡታጅራ ከተማ የተቋቋሙ ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከላት ገበያን በማረጋጋት በኩል ጉልህ አስተዋጾ እያበረከቱ መሆናቸውን ሸማቾች ገለጹ።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ሸማቾች መካከል ወይዘሮ ሰላማዊት ታምሩ እደገለጹት፣ ማዕከላቱ አምራቹን ከሸማቹ ጋር በቀጥታ ስለሚያገናኝ የሚፈልጉትን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዙ ነው።
ሰው ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዲከሰት የሚያደርጉ ህገወጥ ደላሎችን ከግብይት ሥርአቱ እንዲወጡ መደረጉን የምርት አቅርቦቱ እንዲሻሻል ማድረጉንም ተናግረዋል።
የግብይት ማዕከላቱ ምርቶችን በቅርበትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለመግዛት እንዳስቻላቸው የጠቀሱት ወይዘሮ ሰላማዊት፣ በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ይበልጥ ተጠቃሚ በማድረጋቸው እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል።
በከተማው የቀበሌ 02 ነዋሪ ወይዘሮ ሄለን እሸቴ በበኩላቸው የግብይት ማዕከላቱ ገበያው እንዲረጋጋ የራሰቻውን አስተዋጾ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ማዕከላቱ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ በሚያስቡ ነጋዴዎች የሚደረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር እያስቻሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ በበኩላቸው አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ ሦስት ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከላት መቋቋማቸውን ገልጸዋል።
በማዕከላቱ አማካኝነት ለማህበረሰቡ ምርት በቀጥታ እየቀረበ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ማህበረሰቡ በአቅሙ የሚፈልገውን እንዲሸምት ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።
በቀጣይም ተጨማሪ ማዕከላትን በማስፋፋት ህብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው አምራቹንና ነጋዴውን በቀጥታ የሚያገናኙ 134 ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከላት በክልሉ ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025