የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

<p>የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በዲጂታል አማራጮች የተደገፉ ለማድረግ እየተሰራ ነው</p>

Mar 5, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፡-የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና ኢትዮ ቴሌኮም በአካባቢ ጥበቃ ኢኒሼቲቮች ዙሪያ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

የተቋማቱ አመራሮች ለኢኒሼቲቮቹ የዲጂታል እና ቴክኖሎጂ መር መፍትሄዎችን ማበጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተለይም ማህበረሰቡ በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ያለው ተሳትፎን በቴክኖሎጂ ማገዝ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

በቀጣይ ዜጎች የአካባቢ ጥበቃ ህግ ጥሰቶች ሲፈጸሙ ሪፖርት የሚያደርበት መተግበሪያ ለማበልጸግ እንደሚሰራ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.