አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፡-በተያዘው በጀት ዓመት ሰባት ወራት ከእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ወጪ ንግድ ከ63 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢንስቲትየቱ በበጀት ዓመቱ ከእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበርና ወጪ ንግድ 124 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
እቅዱን ለማሳካት ጥራቱን የጠበቀ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት ለአለም ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም መፍጠር ይፈልጋል ብለዋል።
በዚህም ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የእንስሳት ምርቶችን ናሙና በመውሰድ የመፈተሽ እና በዘርፉ ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።
በባለፉት ሰባት ወራት 12ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ለውጪ ገበያ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በዚህም ተቀነባብረው ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ልዩ ልዩ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ከ63 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።
ስጋ እና የስጋ ተረፈ ምርቶች በስፋት ከተላከባቸው የገልፍ ሀገራት መካከል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 45 በመቶውን የሚሸፍን ሲሆን ወደ ሳውዲ አረቢያም ተቀራራቢ የሆነ የምርት መጠን መላክ መቻሉን አክለዋል።
የስጋ ምርት መዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት በአለም አቀፍ የገበያ መድረኮች ላይ የማስተዋወቅና የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን የማሟላት አቅም የሚፈጥር ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ኢንስቲትዩቱ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም 1 ነጥብ 92 ሚሊየን የዳልጋ ከብቶችን በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል ዝርያቸው የተሻሻሉ ጥጆችን ማግኘት የሚያስችል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025