አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2017(ኢዜአ)፦የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስና መቆራረጥ ችግርን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
በቀይ ባህር ውስጥ በሚያልፍ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ መቋረጥ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎታችን በሌሎች አማራጭ መስመሮች ብቻ እየሰራ ነው ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።
በዚህ የተነሳም ሰሞኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስ እና መቆራረጥ እያጋጠመ ይገኛል ብሏል ።
አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ከአገልግሎት አቅራቢዎቹ ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ በመጠየቅም ለደረሰው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025